tg-me.com/Esat_tv1/19309
Last Update:
ጎሮ አካባቢ በተከሰተ የእሳት አደጋ 13 የንግድ ሱቆችና በጋራዥ ዉስጥ የነበሩ አምስት ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደሙ‼️
ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት 6:50 በለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ገብርዔል ቤተክርስቲያን አጠገብ የተነሳዉ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
በእሳት አደጋዉ በቤተክርስቲን ዙሪያ ያሉ 13 የንግድ ሱቆችና በጋራዥ ዉስጥ የነበሩ አምስት ተሽከርካሪዎች ሙሉ ሙሉ የወደሙ እና በጋራዡ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 12 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች 66 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተሰማሩ ሲሆን የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠርም 4 :10 ሰዓት መፍጀቱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እሳቱን ለመቆጣጠር ባደረጉት ርብርብ እሳቱ ወደ-ቤተክርስቲያኒቱ እንዳይዛመት ማድረግ የቻሉ ሲሆን በጋራዡ የነበሩ ቁጥራቸዉ 15 የሆኑ ተሽከርካሪዎችንም ማዳን ችለዋል።በአደጋዉ በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አልመድረሱን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል።
በጋራዡ ውስጥ የነበሩ ተሽከርካሪዎች የያዙት ነዳጅና ሌሎች ፈሳሽ ተቀጣጣዮች እንዲሁም ንግድ ሱቆቹ እሳትን ሊቋቋሙ ከማይችሉ ቆርቆሮና መሰል ግብዓቶች መገንባታቸዉ ለእሳቱ መባባስ አስተዋጾኦ ማድረጉን አቶ ንጋቱ ተናግረዋል።
የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት የሚሰጡ ጋራዦች ደረጃቸዉን በጠበቁ ግብዓቶች የተገነቡና ከንግድ ሱቆች ከመኖሪያ አካባቢዎች የራቁ መሆን እንዳለበት ኮሚሽኑ አስጠንቅቋል።
@Esat_tv1
@Esat_tv1
BY ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
Share with your friend now:
tg-me.com/Esat_tv1/19309